Skip to content
Artwork for Drum of Changes
Society & CultureGovernmentNewsPolitics

Drum of Changes

Zelalem Demissie

From the heart of ancient kingdoms to the pulse of modern cities, a new rhythm echoes across the continent. Africa is rising — a formidable force shaping the world’s future. For generations, Africa has been the most spoken about, yet the least heard. But today, the call is unmistakable: Africa demands its rightful place at the table of global power.

Welcome to 'Drum of Changes' — a program dedicated to the stories that matter to Africa. Here, we explore culture, history, art, politics, the economy, and more, all through the lens of Africa itself. 'Drum of Changes' brings you the voices of transformation resonating across the continent.
Play
  • 28 episodes
  • Avg 58 min
  • English
Counted on this page — what you have heard stays on this device, so it is not something the list can be paged by.
  • S1 · E55
    Saturday · 1 hr

    የአፍሪካ አረንጓዴ ጎህ፡ የማዕድን እሴትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት

    የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሁለት አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። የመጀመሪያው፣ አፍሪካ ከአዳዲስ ዓለም አቀፍ ጥምረቶች እና ከሻንጋይ የትብብር ድርጅት የምታገኛቸውን ትምህርቶች ከወራቤ ዩኒቨርሲቲው የምጣኔ ሀብት መምህር መሐመድ ኢሳ ጋር የምንዳስስበት ነው። ሁለተኛው ደግሞ፣ አፍሪካ ልማትና የድህነት ቅነሳን ሳታስተጓጉል ወደ ንጹሕ የኃይል አማራጭ የምታደርገውን ሽግግር ይመለከታል። በጉዳዩ ላይ ሪቻርድ ሚዩንጊ (ዶ/ር) እና ከተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ማሪት ቅጣው አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል።

  • S1 · E54
    September 17 · 1 hr

    የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት እና በአፍሪካ ሴቶች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ

    በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሩቅ የሚከሰቱ ግጭቶች ከዳካር እስከ ናይሮቢ የቤተሰብ ወጪንና የገበያ እንቅስቃሴን እንዴት እየቀየሩ እንደሆነ ከታዋቂ የመብት ተሟጋች ጋር ዳስሰናል። የዓለም አቀፍ አደጋዎችን አህጉራዊ ተፅዕኖና የሴቶችን የኢኮኖሚ ጫና በጥልቀት የምንመረምርበትን ዝግጅት እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። ለዚህም ናይጄሪያዊቷን የመብት ተሟጋች ፋዴኬሚ አኬንፌዳሪንን አነጋግረናል።

  • S1 · E53
    September 16 · 1 hr

    ከኔቶ ባሻገር፡ ደህንነት፣ ሉዓላዊነት እና አፍሪካ እየተለወጠ ባለው ዓለም ውስጥ ያላት ቦታ

    አሜሪካን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የኢንዶ-ፓስፊክ ስትራቴጂ ኔቶን ወደ አዲስ የውድድር አውድ እንዲገባ እያደረገው ይገኛል። ይህ ደግሞ መረጋጋትን ሳይሆን አዲስ ቅራኔን ብቻ ነው የሚጋብዘው። “አሁን እኮ የኔቶ ዓላማ የጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ መፍጠሪያ እና ማሰፋፊያ ወደ መሆን አዘንብሏል [...] የአፍሪካ ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው በኢኮኖሚ ነፃነት እና በራሷ የንግድ ማዕቀፎች እንጂ ከውጭ በሚመጡ ውሱን እርዳታዎች ብቻ አይደለም […] እኛ አፍሪካውያን የምንፈልገው አካታች የዓለም ሥርዓትን እንጂ አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት ውጥረት አይደለም” በማለት በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ መምህር እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ኔቶ ወደ እስያ-ፓስፊክ የሚያደርገው ስትራቴጂካዊ መስፋፋት ከብሪክስ እያደገ ከመጣው ባለብዙ ዋልታ አስተሳሰብ ጋር እንዴት እንደሚጣጣም በዋናነት ይዳስሳል። መምህር እና ተመራማሪ እንዳለ ንጉሴ በዚህ ጉዳይ ላይ ወቅታዊ ማብራሪያ የሚሰጡን ዕንግዳችን ናቸው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E52
    September 16 · 1 hr

    በብራና የተጻፈ፡ የኢትዮጵያ ሕያው የሥልጣኔ መዝገብ

    የዛሬው የ ድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ትኩረት ከነሓሴ 28፣ 2018 ዓ.ም. እስከ መስከረም 3፣ 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብራና መጻሕፍት ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ላይ ነው። በዚሁ ጉዳይ ላይ የሐመር ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ትንሳኤ ተስፋሚካኤልን እና የፕሮጀክት ማናጀሯን ቃልኪዳን ብርሃኑን አነጋግረናል።

  • S1 · E51
    September 16 · 1 hr

    ከቃል ኪዳን ወደ ትግበራ ኃይል፡ የአፍሪካ የአየር ንብረት አጀንዳ

    በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ከባድ ድርቅና ጎርፍ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ከመፈተኑ ጀምሮ፣ እስከ ታላላቅ የድርድር መድረኮች ቃላት ከድርጊት የሚበልጡበትን አዝማሚያ ጨምሮ፣ አፍሪካ የአየር ንብረት ሉአላዊነቷን ለማስከበር የምታደርገውን የረጅም ጊዜ ትግል ታላቅ ታሪክ አካል አድርገን እናቀርበዋለን። ዝግጅቱን ከ 14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥና ልማት ጉባኤ አንጻር የምናቀርበው ሲሆን፣ በጉባኤ ላይ ተገኝተን ዮሴፍ አመሓን (ዶ/ር)፣ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የአየር ንብረት ተማራማሪ ጨምሮ የተለያዩ ተሳታፊዎችን አውርተናል።

  • S1 · E50
    September 16 · 1 hr

    የአፍሪካ የሰላም መዋቅር፡ የአፍሪካ ህብረትን ሚና ማጠናከር

    የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሦስት ጉዳዮችን ይዳስሳል። በቀዳሚው ጉዳዩ የአፍሪካ ህብረት ከዲፕሎማሲ ውይይት ወደ የዜጎችን ደህነት ጥበቃ የሚቀይርበትን እና የፋይናንስ ጥገኝነትን በመቀነስ የሰላም ስልታዊ አቅሙን የሚያጠናክርበትን መንገድ ይቃኛል። በሁለተኛ ጉዳዩ ኢትዮጵያ የ 2029 ኙን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ይዳስሳል። ለዚህም የብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑን ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጂራ አነጋግሯል። በሦስተኛው ጉዳዩ ደግሞ ጳጉሜን 1 የጀመረውንና እስከ ጳጉሜን 5 የሚዘልቅዉን ፌስቲቫል ይቃኛል።

  • S1 · E48
    September 2 · 1 hr

    የሳህል ህብረት ስልታዊ የሉዓላዊነት እንቅስቃሴ፦ የቀጠናዊ ኃይልን ትርጉም እንደገና መበየን

    “ካፒታሊዝም [የምዕራቡ] በመሰረታዊነት የተመሰረተው በኢኮኖሚ ብዝበዛ ላይ ነው [...] አሁን የቀድሞ የፈረንሳዪ ቅኝ ግዛቶች «የቅኝ ግዛት መገበያያን» አንጠቀምም ባሉ ጊዜ የነዚህ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እስከ ፖለቲካዊ ግድያዎች ድረስ ገጥሟቸዋል። ምክንያቱ ደግሞ «የቅኝ ግዛት መገበያያዎች» ለአውሮፓውያኑ የአመት ገቢያቸው ነው፣ የአፍሪካን ገበያ የሚቆጣጠሩበት ነው” ሲሉ እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት ወደ ቀጠናዊ ሉዓላዊነት ቁርጠኛ ሽግግር እያደረገ ወደሚገኘው የሳህል ቀጠና ይወስደናል። ለዚህም በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑትን እንደለ ንጉሴ አውርተናል። ድረም ኦቭ ቼንጅስ በሁለተኛው ጉዳዩ፣ የሀገርበቀል የሰላም ጥረቶች ተምሳሌት የሆነው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር መድረክ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊ መፍተሄዎች ከመፍታት አንፃር የሚኖረዉን ትርጉም እንቃኛለን። ለዚህም የፌዴራል ጥናቶች ተመራማሪና የምክክር ሂደቱ ተሳታፊ ኃይለኢየሱስ ታዬ (ዶ/ር)እና የሐይማኖት መምህር እናየምክክር ሂደቱ ተሳታፊ ቀነዐ ለሚን እንግዳ አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E47
    September 2 · 1 hr

    የዓለም አቅፉ ደቡብ አዲስ ጎህ እና የብዙ ወገንተኝነት ጉዞ

    እያደገ የመጣው የብሪክስ እና የዓለም አቅፉ ደቡብ አገራት ህብረት ዓለምን ወደ እውነተኛ ሉዓላዊ፣ የጋራ እኩልነትና የብዙ ወገንተኝነት ሥርዓት ከፍ የሚያደርግ ታሪካዊ ምዕራፍ እየፈጠረ ይገኛል። “የዓለም አቅፉ ደቡብ ምዕራባውያንን እንዲሁም አሜሪካንን በእርግጥኝነት የመገዳደር ቁመና ላይ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር የዓለም አቅፉ ደቡብ ሀገራት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እያንዳንዱ ሉዓላዊ ሀገር በልኩ የሚወከልበት መድረክ እንዲሆን ይፈልጋሉ […] ብሪክስም የጸጥታው ምክር ቤት ቦታን ለመረከብ የሚያስችል የአለም አቅፉ ደቡብ ትልቅ አቅም ሆኖ ሊመጣ ይችላል” ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በዓለም አቀፍ ፖሊሲ ልማት እና ዲፕሎማሲ ዙሪያ የሚያጠነጥን ሲሆን፣ በወቅታዊ የጂኦፖሎቲካዊ ቀውሶች፣ የንግድ ጦርነቶች እና በዓለም አቀፉ ደቡብ የአጋርነት ጥረቶች ላይ ያተኩራል። በዚህ ሰፊ ረእስ ዙሪያ ለምናደርገው ውይይት ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ ያደረኝ ሲሆን፣ ቆይታችን ያደረግነውም በአዲሱ መጽሐፋቸው "ታሪፍስ ኤንድ 'ኒክሌር' ትርትስ ኦፍ ኤ ኒው ኮልድ ዎር፡ ዘ ግሎባል ሳውዝስ ክዌስት ፎር መልቲላተራሊዝም” ዙሪያ ባሉ ሀሳቦች አውድ ውስጥ ነው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E46
    August 17 · 1 hr

    ቻድ ከአይ.ሲ.ሲ ለመውጣት ያሳለፈችው ውሳኔ፡ የምዕራቡ ዓለም መሣሪያ ለሆነው ተቋም የአፍሪካ ምላሽ?

    "የምዕራቡ ዓለም የዓለም አቀፉን የወንጀል ፍርድ ቤት (አይ.ሲ.ሲ) የራሱን ፍላጎት ማስፈፀሚያ ያደረገው ይመስላል [...] ቻድ ከ አይ.ሲ.ሲ ለመውጣት ያሳለፈችው ውሳኔም ለቀሪው የአፍሪካ አህጉር ግልጽ መልዕክት አስተላልፏል 'አፍሪካ የራሷን ዕድል በራሷ የመወሰን እና የራሷን የፍትህ መንገድ የመቀየስ ጊዜዋ አሁን ነው' የሚል" ሲሉ የሕግ ባለሞያው መታገስ ዉለታው ለስፑትክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ዝግጅታችን ቻድ ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይ.ሲ.ሲ) ለመውጣት የወሰደችውን ርምጃ መነሻ አድርገን የተቋሙን መዋቅራዊ አድልዎ እና በአፍሪካ የሀገርበቀል የፍትህ ስርዓቶችን የመገንባት ጥረቶችን በጥልቀት እንፈትሻለን። ለዚህም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህር እና የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ መታገስ ዉለታው ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ጉዳያችን ደግሞ፣ እ.ኤ.አ ከሐምሌ 29 እስከ 30፣ 2026 በአዲስ አበባ የተካሄደውን ወርልድ ፐብሊክ ፎረም መነሻ አድርገን፤ የግብርና ዘርፉን ወደ 21ኛው ክፍለ ዘመን በማሸጋገር ረገድ የዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ሚና እንቃለን። ይህንን ጉዳይ የበለጠ እንዲያብራሩልን ከሩሲያው "ግራሚዮን ፕላስ" ኩባንያ ተወካይ ፓቬል ኮኖቭ ኒኪታ ጋር ተወያይተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E45
    August 6 · 1 hr

    የኤደን ባሕረ ሰላጤ፡ የባሕር ወንበዴዎች እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ አስፈላጊነት

    የዓለም አቀፉ የባህር ላይ ጉዞ ድርጅት በሶማሊያ የባህር ዳርቻ እና በኤደን ሰላጤ ላይ የባህር ላይ ወንበዴዎች ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ "አሳሳቢ ነው" ብሏል። “ሩሲያ ትራዲሽናል (ባህላዊ) የኢትዮጵያ አጋር ነች ስንል መንግስታት ቢቀያየሩ እንኳን የማይቀያየር ወዳጅነት ነው ያላቸው ማለት ነው። የአድዋን ጦርነት ብናነሳ እንኳን [ከኢትዮጵያ ጋር የቆመች] ብቸኛዋ የአውሮፓ ሀገር ነች አይደለም? [...] ለአፍሪካውያንም እኮ ከሩሲያ የሚቅድም ወዳጅ የለም [...] ዛሬ ሩሲያ የባለብዙ ዋልታ ዓለም ስረዐት ወሳኝ አካል መሆኗ ወደአንድ ወገን አዘንብሎ የነበረውን የአዓለም ግንኙነት ስረዓት ሚዛን ለማስጠበቅ አስችሏል” ሲሉ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ እንዳለ ንጉሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው ድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ያላትን የጠበቀ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሠረት በማድረግ በኤደን ሰላጤ ላይ የባህር ላይ ውንብድናን ለመከላከል ልትጫወት የምትችለውን ስልታዊ ሚና እንቃኛለን። ለዚህም በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እንደለ ንጉሴ እንግዳችን ናቸው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E41
    August 3 · 1 hr

    ታላቁ አሰላለፍ:- የአፍሪካ መንገድ በአዲሱ የባለብዙ ዋልታ ዘመን

    "ዓለም አቀፉ ደቡብ አሁን ከቡድን 7 በበለጠ የዓለምን ኢኮኖሚ በበላይነት እየተቆጣጠረ ነው [...] አዲስ የገንዘብ ሥርዓት ማለት፡ የዶላር ተፅዕኖን የመቀነስ ሂደትን ያፋጥናል፣ አሜሪካ ዶላር በእጇ በመሆ ምክንያት በሀገራት ላይ የምትጥለው ማዕቀብ ታሪክ ሆኖ እንዲቀር ያደርጋል” ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሞያ እና የፖሊሲ አማካሪ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ኢኮኖሚያዊ መሰናክሎችን በግንባር ቀደምትነት እየደረደሩ ባሉበት እና ነባር ባለብዙ ወገን ስምምነቶችን ስጋት ላይ በሚጥሉበት በዚህ ወቅት፣ ጠለቅ ያሉ ሁነቶችን መረዳት ለአፍሪካ ስትራቴጂካዊ የወደፊት ጉዞ የሚኖረውን ወሳኝነት እና ከዚህም አንፃር የታዳጊ ኢኮኖሚ ባለቤቶች የሚኖራቸውን የፖሊሲ አማራጮች በጥልቀት እንመረምራለን። ቆስጠንቲኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪነት ያገለገሉ፣ በአፍሪካ ህብረት የፀረ-ሙስና ቦርድ መሪነት የቆዩ ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሞያ እና የፖሊሲ አማካሪ ሲሆኑ፣ በቅርቡም “ታሪፍስ ኤንድ ‘ኒዉክሌር’ ትሬትስ ኦቭ ኤ ኒዉ ኮልድ ዎር” የተሰኘ አዲስ መጽሐፋቸው ልንባብ አብቅተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E40
    July 18 · 1 hr

    ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት፦ የሩሲያ አፍሪካ ግንኙነት ለፍትሐዊ የዓለም ስርዓት

    “ባለብዙ ዋልታ የዓለም ስረዓት መፈጠር በተለይም ለአፍሪካ አማራጭ የሌው ጉዳይ ነው [...] ሩሲያም ይህንን ነገር ይዛ መቅረቧ አስፈላጊ ነው [...] ሰርጌ ላቭሮቭ ያንሱት እና ስለአፍሪካ ሁለንተናዊ ነፃነት የሚያወሳው ‘የአፍሪካ ዳግም መነቃቃት’ አፍሪካውያን የምንቀበለው ሲሆን፣ ሩሲያ ፍትሃዊ የዓለም ስረዓት እንዲፈጠር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው” ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አስራት ኤርሞሎ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ በቀዳሚነት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 7 እስከ 10 ቀን 2026 በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ያደረጉትን ከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶ መነሻ አድርገን የይፋዊ የሥራ ጉብኝቶቹን ስትራቴጂካዊ አንድምታዎች እንቃኛለን። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ሐሳባቸዉን የሚያጋሩን በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር መምህር፣ ተማራማሪ ዶ/ር አስራት ኤርሞሎ ናቸው። በተከታዩ ጉዳያችን ደግሞ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 15 ቀን 2026 የጀመረዉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ሂደት በተመለከተ ከብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) ጋር የተደረገን አጠር ያለ ቆይታ ይዞላችሁ ይቀርባል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  • S1 · E39
    July 11 · 1 hr

    የአፍሪካና ሩሲያ የጋራ ህልም፤ ወደ ባለብዙ ወገን ዓለምአቀፋዊ ሥርዓት

    የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላፍሮቭ ከሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 3 1ቀን 2018 ዓ.ም በአፍሪካ ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በቡሩንዲ አጠናቅቀዋል፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የሰርጌላቭሮቭን ይፋዊ የስራ ብዙ የአፍሪካ አገራት የዩኒፖላር ሥርዓትን ለመግታት ወደ ሩሲያ እንደሚመለከቱ ተናግረዋል። “በምዕራባውያን የበላይነት የሚመራው የዩኒፖላር (የአንድ ወገን) ሥርዓትና መዋቅራዊ ማስተካከያ ፕሮግራሞች (ስትራክቸራል አድጀስትመንት ፕሮግራምስ) በአፍሪካና በተቀረው ዓለም ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድረዋል” ሲሉ በላይ በየነ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር በላይ በየነን አነጋግረናል። በዚሁ ዝግጅት ሁለተኛው ክፍል በሶሻሊስት የአውሮጳ ሀገራት ውስጥ ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ኢትዮጵያውያንን አበርክቷቸውን ለመዳሰስ ከቀድሞ የሶሻሊስት ሀገር ተማሪና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ሰለሞን አሊ (ዶ/ር) ጋር ሰፊ ዉይይት አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E38
    July 11 · 1 hr

    የመጨረሻው ምሽግ፦ በአገር በቀል ዘሮችና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ የተጋረጠው አደጋ በአፍሪካ

    “በምዕራባውያን አምሳል የተነደፉ የግብርና ምርምር ተቋማት፣ የአገር በቀል የእህል ዘሮቻችን አዋጭነትን ዝቅ አድርጎ የመመልከት ዝንባሌ አለባቸው። ነገር ግን እውነታው ዘሮቻችንን ያጣን ዕለት ማንነታችንን የማጣታችን ጉዳይ ነው። በአሁኑ ወቅት እነዚህ የውጭ ኃይሎችና ግዙፍ ኩባንያዎች ሁሉንም ነገር ተቆጣጥረውታል። በአፍሪካ እስካሁን እጃቸውን ያላስገቡበት ብቸኛው ዘርፍ ቢኖር ምግባችንና የምግብ ስርዓታችን ብቻ ነበር። አሁን አሁን ይሄንኑ የመጨረሻ ምሽጋችንን ለመቆጣጠር በከፍተኛ ፍጥነት እየመጡ ነው” ሲሉ ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በሩቅ ባሉ ኃይሎች መካከል የሚቀሰቀሱ ግጭቶች እንደምን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን የዕለት ጉርስ ላይ ስጋት እንደሚሆን እንመረምራለን፤ ይህ ሁኔታም የምግብ ዋስትና በሎም ዋነኛ የብሔራዊ ደህንነት እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ የመሆኑንም ነገር ያስቃኘናል። ለዚህም የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥምረት ዋና አስተባባሪ የሆኑትን ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E37
    July 8 · 1 hr

    የላቭሮቭ ይፋዊ የስራ ጉብኝት፡ ኢትዮጵያ ፣ ብሪክስ እና ባለብዙ ዋልታው ዓለም

    "ሩሲያ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ መልካም ወዳጅ ሆና ለዘመናት ቆይታለች። በተቃራኑው ደግሞ የምእራቡ አለም፣ አፍሪካን በማሳነስ በምእራቡ ላይ ጥገኛ ሆና እንድትቀር እየሰራ ይገኛል [...] ሩሲያ ግን የአፈሪካን ራስን የመቻል ፍላጎት በመሰረታዊነት የተረዳች ሀገር ነች" ሲሉ የሕግ ባለሞያ እና የዓለም ማቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ ብሩክ መላኩ ለስፑትኒክ ካፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚነት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭን የኢትዮጵያ ጉብኝት አንስተን ሁለንተናዊ አንድምታዎቹን እንቃኛለን። ለዚህም የሕግ ባለሞያ እና የዓለም ማቀፍ ፖለቲካ ተንታኝ ብሩክ መላኩን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጉዳያችን በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ ያደረግን ሲሆን፣ የቅኝ ግዛት ውርስ የሆነው የ"ሉዓላዊነት" እሳቤ በአፍሪካ ያመጣቸውን መዘዞች እንቃኛለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E36
    June 15 · 1 hr

    የተዘረፉ ቅርሶች፡ የአፍሪካን የታሪክ እውነት ለማስመለስ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ትግል

    “[…] ከአፍሪካ በጉልበት የተወሰዱ የተለያዩ ቅርሶች ለአፍሪካውያን ባለቤቶቻቸው ሳይመለሱ በአውሮፓ ሙዚየሞች እንዲቆዩ የሚደረገው ደህንነታቸው በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅ ነው የሚለው መከራከሪያ እውነታነት የለውም። ምክንያቱም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሙዚየሞች በጦር መሳሪያውች ተደብድበዋልና። በቅርቡ በፈረንሳዩ ሉቭር ሙዚየም ጭምር በርካታ ስርቆቶች ተፈጽመዋል። ስለዚህ በምዕራቡ አገራት ያሉ ሙዚየሞች በሙሉ አስተማማኝ ናቸው ማለት አይቻልም” ሲሉ የማህበራዊ ጉዳዮች ተመራማሪው አሉላ ፓንከረስት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን በቀዳሚ ጉዳዩ፣ የአፍሪካን የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ትክክለኛ መኖሪያቸው ለመመለስ የሚደረገውን ታሪካዊ፣ ስልታዊ እና ጥልቅ ስሜት የሚንጸባረቅበትን አፍሪካዊ እንቅስቃሴ ያስቃኘናል። ለዚህም የማህበራዊ ጉዳዮች ተመራማሪውን አሉላ ፓንከረስት (ዶ/ር) አነጋግረናል። እ.ኤ.አ. ሰኔ 12 እና 12 ቀን 2026 በአዲስ አበባ የተካሄደው አንደኛው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ እና የቴክኖሎጂ ውድድር ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የምንቃኝበት ሁለታኛው ጉዳያችን ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ ሐሳባቸዉን ሊያጋሩን ብሩክ ከድር (ዶ/ር)፣ አናንድ አንባላጋን እና ፋራይ ቺዳሩን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E35
    June 4 · 1 hr

    ሴንት ፒተርስበርግ ዓለምዓቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም፣ ለአፍሪካ ምን አማራጮችን ይዞ መጥቷል?

    "አፍሪካ ከዚህ ጉባኤ [ከ ሴንት ፒተርስበርግ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክ ፎረም] ትጠቀማለች [...] አሜሪካ በኢራን፣ በሩሲያ እና በሌሎች ሀገራት ላይ የጣለቻቸው ማዕቀቦ ምዕራባውያኑ በፋይናንስ አስተዳደር ረገድ እምነት የሚጣልባቸው አጋሮች ሊሆኑ እንደማይችሉ እያሳየ ጉዳይ ነው። በዚህም ምክንያት ሀገራት የዕዳ ቀውስን ለመፍታት ጨምሮ ለራሳቸው የሚበጀ የተሻለ ጎዳናነ መሻት ይኖርባቸዋል [...] ጉባኤው ከዚህ አንፃር ፋየዳው የጎላ ነው" ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። የዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ቀዳሚው ጉዳይ እ.ኤ.አ. ከ ሰኔ 3 እስከ 6 በሩሲያዋ ሴንት ፒተርስበርግ እየተካሄደ ባለው ሴንት ፒተርስበርግ ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክ ፎረም 2026 ላይ ያተኩራል፡፡ ''ለአፍሪካስ ምን አማራጮችን ይዞ ይመጣል?'' ስንል እንጠይቃለን። በጉዳዩ ላይ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያውን ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) አነጋግረናል። በሁልተኛው ጉዳያችን ደግሞ የታንዛንያ ፕሬዝደንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን የሩሲያ ጉብኝት አንድምታዎች በስፋት እንዳሰሳለን። ለዚህም ታንዛንያውያን የምጣኔ ሀብት እና የዓለም አቅፍ ፖለቲካ ተንታኞችን አነጋገርናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E34
    May 25 · 1 hr

    የአፍሪካ ቀን እና የአንድነቱ መሐንዲሶች፡ የታሪክ አሻራ እና የዲፕሎማሲ ጉዞ

    “የአፍሪካውያን ማንነታችንን የምናከብርበት ብቸኛው ቀን ይህ [የአፍሪካ ነፃነት ቀን] በአህጉር ደረጃ ሊከበር የሚገባው ይመስለኛል። ትርጉሙን አባቴ [ከተማ የፍሩ] ያደረገውን፣ ኳሜ ንክሩማህ እና አፄ ኃይለ ሥላሴ ያከናወኑትን ማስታወስ ይኖርብናል” ሲሉ መኮንን ከተማ ይፍሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በየዓመቱ ግንቦት 17 ወይም እ.ኤ.አ ግንቦት 25 የጋራ ጉዟችንን እና ቅርሳችንን ለማክበር በመላው አፍሪካ የሚታሰበው ታሪካዊው የአፍሪካ ቀን ሆኖ ይከበራል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ በጥልቅ ተከፋፍላ የነበረችውን አፍሪካ በአንድ ሰንደቅ ዓላማ ስር ያሰባሰበውን ስትራቴጂካዊ ጥበብ ለመረዳት በአህጉሪቱ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያለውን ያንን ወሳኝ ወቅት መለስ ብለን እንቃኛለን። ለዚህ የእውቁ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት ልጅ እንዲሁም ጸሐፊ የሆኑትን መኮንን ከተማ ይፍሩን ጋብዘናል። በሁለትኛው ጉዳያችን ደግሞ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሳሰረ በመጣው ዓለም ውስጥ የአፍሪካን ባህል፣ ማንነት እና የታሪክ ባለቤትነትን የመጠበቅ ወሳኝ የትግል አውድን እንመለከታለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  • S1 · E34
    May 21 · 1 hr

    የአፍሪካ ቀን፦ በትውስታ፣ በትርጉሙ እና ባልተጠናቀቀው የአንድነት ጉዞ መካከል

    የአፍሪካ ቀን የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት በፈረንጆቹ ሚያዝያ 25፤ 1963 የተመሰረተበትን ቀን የሚዘክር እለት ነው፤ በየዓመቱም ይከበራል። “የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ወቅት የነበረው የአንድነት መንፈስ በዛሬዪቱ ተቀዛቅዟል [...] የአፍሪካ ነፃነት ቀንም የፍሪካን ነፃነት እያከበርን፣ ስለአፍሪካ እጣፈንታ ኮስተር ብለን የምንወያይበት እለትም ሆኖ ማለፍ ነው ያለበት”ሲሉ የአፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዋና ዳይሬከተር አሮን ስይፉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ፣ የነፃዪቱ አፍሪካ ተላሚዎች፣ አባቶች ያለሟትን አፍሪካ ዛሬ ካለችበት ሆነን እንቃኛታለን። አሮን ሰይፉ፣ የአፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ሶሳይቲ ኦርጋናይዜሽን መስራች እና ዋና ዳይሬከተር በመረጥነው ርእስ ዙሪያ ሀሳባቸውን አጋርተውናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

  • S1 · E33
    May 5 · 1 hr

    85ኛው የአርበኞች ድል በዓል፡- የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ክህደት እና የኢትዮጵያ ጽናት

    ኢትዮጵያ 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን ፣ 2018 ዓ.ም አክብራለች፡፡ ''በወቅቱ የአውሮፓ ኃያላን ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ያጡትን ካፒታልና ሀብት መልሶ ለማግኘት አፍሪካን እንደ ግብዓትና የጉልበት ምንጭ ተጠቅመዋል። ጣሊያን በ1889 በዓድዋ ጦርነት የደረሰባትን ሽንፈት ለመቀልበስና የኢንዱስትሪ አብዮቷን ለመደገፍ ኢትዮጵያን በሙሉ አቅሟ ለመቆጣጠር መጣች። [...] የሊግ ኦፍ ኔሽንስ በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ወረራ ማስቆም አልቻለም። እንዲያውም የድርጅቱ አባል የሆኑት እንደ ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት በዲፕሎማሲው ረገድ ለጣሊያን መንገድ ከፍተዋል።" ሲሉ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥናትና ምርምር ባለሙያ አብዲ ወርቅነህ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የድረም ኦፍ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ የፋሺስት ጣሊያን ዳግም ወረራ ምክንያቶች፣ የአውሮፓ ኃያላን በአፍሪካ የነበራቸው የተዛባ ፍላጎት፣ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ የዲፕሎማሲ ውድቀት እና የኢትዮጵያ አርበኞች ለአምስት ዓመታት ያሳዩትን ጽናትና በድል የተጠናቅቀውን ድል አስመልክቶ ፣ የታሪክ ምሁሩ ጥላሁን ጣሰው እና በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የጥናትና ምርምር ባለሙያ አብዲ ወርቅነህን አነጋግረናቸዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

Showing 1–20 of 28 episodes